ስለ እኛ About us
ምስረታ፣ ራዕይ፣ ዓላማ እና እንቅስቃሴዎች
Founding, vision, objectives and activities
የድልድይ አመሠራረት Founding of Dildiy
ለግማሽ ምዕተ ዓመት በኢትዮጵያ ሰፍኖ የቆየው የአንድ ፓርቲ አመባገነናዊ አገዛዝ ያስከተለው የዴሞክራስያዊ መብቶች መታፈንና የሰብአዊ መበቶች መረገጥ የኢትዮጵያን ህዝቦች አንድነትና የአገሪቱን ህልውና አደጋ ላይ `በመጣሉ፣
በኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በተለያየ ደረጃ ተሳትፎ በነበራቸውና አሁንም ባላቸው ኢትዮጵያውያንና የኢትዮጵያ ወዳጆች የተመሠረተ የመወያያ መድረክ ነው። ፎረሙ ተመሳሳይ ፍላጎትና ዓላማ ባላቸው ኢትዮጵያውያን በሀምሌ ወር 2015 ዓም በፍርንክፈርት በተካሄደው የኢትዮጵያውንያን የባህልና የስፖርት ፌሲቫል ላይ የተጠነሰሰ በመሆኑ፣ ፎረም ፍራንክፈርት ተብሎ ተሰየመ፡፡ ይሁንና ከዚያ በኋለ አባላቱ ስሙን አሻሽለው በአውሮፓ የኢትዮጵያዊያን መድረክ ድልድይ፣ አትራፊ ያልሆነ ድርጅት፣ FEE (Forum des Ethiopiens en Europe) በሚል በ12/03/2017 በብሩሰል፣ በቤልጅግ ሕግ ተመዝግቦ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል፡፡
The prevalence of a dictatorial one party state and suppression of democratic and human rights for decades endangered the unity of the Ethiopian people and undermined the legitimacy of the state. The shared values of the Ethiopian people accumulated through long years of living together were being seriously eroded. As a result, Ethiopians and friends of Ethiopia with varying political and organizational backgrounds, past and present came together and created the Forum as a politically non-affiliated, independent platform for discussion.
The idea of creating a discussion forum was initially floated in Frankfurt at the annual sports and cultural festival of Ethiopians in Europe in July 2015, and the name adopted originally was Frankfurt Forum. Later, its name was changed to Forum of Ethiopians in Europe (Forum des Ethiopiens en Europe) and registered under Belgian law as a non profit organization (ASBL) on 12 March 2017.
ራእይ Vision
የሕግ የበላይነት የሰፈነባት፣ ህዝቦቿ በሙሉ በእኩልነት፣ በወንድማማችነትና እህትማማችነት፣ በአንድነትና በሰላም የሚኖሩባት ዴሞክራሲያዊት ኢትዮጵያ እውን መሆን፡፡
The realization of a democratic Ethiopian state where the rule of law prevails and all the peoples of Ethiopia live together in peace as equal sisters and brothers.
ዓላማ Objectives
- ዴሞክራሲያዊና ፍትሓዊ ሥርዓት በኢትዮጵያ እውን እንዲሆን አስተዋጽኦ ማድረግ፣
- በሀገራችን ችግሮች ዙሪያ ያተኮረ የሰከነና መደማመጥ የሰፈነበት ውይይት ማበረታታት፣
- የተለያዩ አስተሳሰቦች የሚንጸባረቁበት ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ሥርዓት እንዲዳብር ማገዝ፣
- የአብሮ መኖር ባህላችንንና እሴቶቻችንን መንከባከብ፣ ማስተዋወቅ፣
- የተፈጥሮ ሀብትን ለሚንከባከብና ማህበራዊ ፍትህን ላካተተ ዘላቂ ልማት ትኩረት መስጠት፡፡
- Contribute toward the realization of a just and democratic society;
- Encourage open, tolerant and mature discussion on the problems facing our country;
- Encourage the development of a pluralist political order;
- Preserve and promote our cultural assets of togetherness;
- Promote a culture of social justice and environmental protection.
ተግባር Activities
- የውይይት መድረኮችን ማዘጋጀት፣
- የዴሞክራሲ፣ የሕግ ልዕልና እና የሰብአዊ መብት መርሆዎችን ማስተዋወቅ፣
- የዲሞክራሲ ሥርዓት መሠረተ ሃሳቦችን እና በሕግ የመገዛትን ጽንሰ ሃሳቦች ማስፋትፋት፣
- በአባሎች ወይም በሌሎች ባለሙያዎች የተዘጋጁ ጥናት ላይ የተመሠረቱ የምርምር ጥናቶችን፣ ትንተና የያዙ ጽሁፎችን ለንባብ ማቅረብ እና በድረ ገጻችን ላይ ማውጣት፡፡
- Organize discussion forums;
- Promote the principles of human rights, rule of law and democracy;
- Promote studies and publications on Ethiopia;
- Promote relevant research works and publications by posting them on the forum’s website.